የሥጋ ደዌ በሽታ

Written by Dr. Samrawit Wondwossen (Medical intern at Myungsung Medical College)

Reviewer: Dr. Nafkot Girum (Assistant professor of Dermatovenereology)

 

የሥጋ ደዌ ምንድን ነው?

የሥጋ ደዌ በሽታ “ማይኮባክቲሪየም ሌፕራ” በተባለ ባክቴሪያ የሚመጣ ኢንፌክሽን ነው :: 

በሽታው ነርቮችን ቆዳንእና አይንን ሊጎዳ ይችላል :: ይህ በሽታ  የተጎዱ አካባቢዎችን “የመነካት፣ ሙቀት እና ቅዝቃዜ የመለየት እና የህመም” ስሜት እንዳይሰማቸው የሚያደርግ ሲሆን እስከ መቆረጥ ወይም የመቃጠል አይነት ጉዳቶች ሊያምራ ይችላል :: 

ባክቴሪያው ነርቮችን ሲያጠቃ ከቆዳው በታች ማበጥን፣ የቆዳ ነጣ ማለትን እና የነርቭ እብጠትን ሊያስክትል ይችላል :: ነርቮቹ ህክምና ካልተደረገላቸው ሰውነታችን የተጎዱትን ጣቶች በመሟጠጥ የእግር ወይም የእጅ ጣቶችን ማጣት አልያም ሽባነትን ሊያስከትል ይችላል :: የፊት ነርቮች ከተጎዱ ደግሞ ዓይነ ስውርነት ሊያስክትል ይችላል :: 

 

 

ሰዎች እንዴት በሥጋ ደዌ ይያዛሉ እንዴትስ ይተላለፋል?

  • በበሽታው ለመያዝ ለብዙ ወራት ካልታከመ የሥጋ ደዌ ታማሚ ጋር ረጅም የቅርብ ግንኙነት መኖር ያስፈልጋል::
  • የሥጋ ደዌ ካለበት ሰው ጋር በአጋጣሚ በመገናኘት የሥጋ ደዌ በሽታ አይተላለፍም:: 
  • እጅ ለእጅ በመጨባበጥ ፣ በመተቃቀፍ ፣ አውቶቡስ ላይ አጠገብ ለአጠገብ በመቀመጥ ወይም ምግብ አብረው በመብላት አይተላለፍም:: 
  • በጾታዊ ግንኙነት አይተላለፍም::
  • በተጨማሪም በእርግዝና ወቅት ከእናት ወደ ፅንስ ልጇ የመተላለፍ እድሉ ዝቅተኛ ነው::

 

ምልክቶች

ምልክቶቹ በዋናነት በቆዳ፣ በነርቭ እና በሰውነት ላይ የሚገ ክፍት ቦታዎች ውስጥ ለስላሳ እና እርጥብ ቦታዎች (mucous membrane) ላይ ተጽዕኖ ያሳድራሉ::

 

የቆዳ ምልክቶች

  • በቆዳ ላይ ነጣ ነጣ ያሉ ስሜት አልባ ምልክቶች( በመቀመጫ እና ቀዝቃዛማ የቆዳችን አካባቢዎች ላይ)
  • በቆዳ ስር ላይ እብጠቶች
  • ህመም የሌላቸው ቁስሎች
  • ህመም የሌለው እብጠት  (ፊት ወይም ጆሮ ላይ)
  • የቅንድብ መጥፋት

 

በነርቮች ላይ በሚደርስ ጉዳት ምክንያት የሚመጡ ምልክቶች

  • የተጎዱ የቆዳ አካባቢዎች ስሜት አልባ መሆን
  • የጡንቻ ድክመት ወይም ሽባነት
  • ዓይነ ስውርነት (የፊት ነርቮች ሲጎዱ)

 

በሽታው እንዴት ነው የሚታወቀው?

  • ከተለመደው ቆዳ ነጣ ያሉ ንጣፎች በመኖር
  • ከቀዘቃዛማ የቆዳችን ክፍሎች ወይም ከእባጮች የሚወሰድ ምርመራ (slit skin smear)

 

በሽታው እንዴት ይታከማል?

  • በተመሳሳይ ጊዜ በሚያገለግሉ 3 የአንቲባዮቲኮች ጥምረት ይታከማል::
  • ሕክምናው ብዙውን ጊዜ ከ6 ወር እስከ 1 ዓመት ይቆያል::  
  • ህክምናው በታዘዘው መሰረት ከተጠናቀቀ ህመሙ የመዳን እድሉ ክፍተኛ ነው::

 

References

EMSA Digital Library

online platform where you can find resources

Fellowship Opportunities

International Opportunities For Young Leaders

ከአእምሮ ጤና ጋር በተያያዘ ድንገተኛ እርዳታ ካስፈለግዎ

በነዚህ ቁጥሮች እርዳታ ያግኙ

Subscribe