አመታዊ የጤና ምርመራ

አመታዊ የጤና ምርመራ በተለያየ የዕድሜ ክልል ላይ ላሉ ሰዎች የሚደረግ እና ለአንድ በሽታ የመጋለጥ
እድላቸውን ቀድሞ ለማወቅ የሚያስችል የምርመራ ዘዴ ነው።
እድሜ እና ፃታን መሠረት አድርገው በየአመቱ እና ከዛም በላይ ሊደረጉ የሚገቡ የምርመራ አይነቶች አሉ።
እነዚህን ምርመራዎች መረዳት እና መቼ መጠየቅ እንዳለቦት ማወቅ ጤናማ ሆነው እንዲቆዩ ያግዝዎታል።
እንደ ካንሰር እና አንዳንድ በቅድመ ጥንቃቄ ልንከላከላቸው የምንችላቸውን ህመሞች ለመቆጣጠር ቀደም
ብሎ ማወቅ በጣም አስፈላጊ ነው።
ጤናማ በሚሆኑበት ጊዜ ምን ዓይነት ምርመራዎችን ማድረግ አለብዎት? ምን ዓይነት ምርመራዎችስ ሃኪምዎ
ሊይዝሎት ይችላል?

እድሜዎ ከ 18- 39 አመት ከሆነ

በዚህ እድሜ ላይ የሚገኙ ወጣቶች አብዛኛውን ጊዜ በትምህርት፣ በስራ እና ቤተሰብን በማስተዳደር
የተጠመዱ በመሆናቸው አመታዊ የጤና ምርመራዎች ብዙ ጊዜ ሳይደረጉ ያልፋሉ።
● ክብደት እና ቁመት
● የደም ግፊት ልኬት
● የዓይን ምርመራ
● የጆሮ ምርመራ
● አጠቃላይ የደም ህዋሶች ምርመራ
● መሰረታዊ ወይም የተሟላ የሜታቦሊክ ፓነል (የኩላሊት አሰራር፣ የጉበት አሰራር ምርመራዎች፣
የተለያዩ የደም ውስጥ ንጥረ ነገሮች ምርመራ)
● የኮሌስትሮል ፍተሻ፡- HDL እና LDL ኮሌስትሮል
● የታይሮይድ ሆርሞን ምርመራ
● የስኳር በሽታ ምርመራ፡
● በ ደም ንክኪና በግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚተላለፉ ኢንፌክሽኖች፡- ኤችአይቪ (HIV)፣ HPV፣
ጨብጥ፣ቂጥኝ ወይም ሌሎች ኢንፌክሽኖችን ሊያካትት ይችላል።
● የሽንት ምርመራ
● የልብ ምርመራ
● የሆድ አልትራሳውንድ
ለሴቶች ተጨማሪ ምርመራዎች
● የማህፀን በር ካንሰር ምርመራ፡ በየ 3 አመቱ የፓፕ ስሚር ምርመራ ያደርጋል (ከ21 ዓመት ዕድሜ
ወይም ግንኙነት ማድረግ ከተጀመረበት ከ3 ዓመታት ጀምሮ)።

እድሜዎ ከ 40 አመት በላይ ከሆነ

በዚህ እድሜ ለተለያዩ በሽታዎች የመጋለጥ እድልዎ ይጨምራል። ስለዚህ ሃኪምዎ አመታዊ የሕክምና
ምርመራ እንዲያደርጉ ይመክራሉ። ይህም ጠቃሚ መረጃ የሚሰጡ ተጨማሪ ምርመራዎችን ማለፍ
ይጠይቃል።
● ክብደት እና ቁመት
● የደም ግፊት ልኬት
● የዓይን ምርመራ
● የጆሮ ምርመራ
● አጠቃላይ የደም ህዋሶች ምርመራ
● መሰረታዊ ወይም የተሟላ የሜታቦሊክ ፓነል (የኩላሊት አሰራር፣ የጉበት አሰራር ምርመራዎች፣
የተለያዩ የደም ውስጥ ንጥረ ነገሮች ምርመራ)

● የኮሌስትሮል ፍተሻ፡- HDL እና LDL ኮሌስትሮል
● የታይሮይድ ሆርሞን ምርመራ
● የስኳር በሽታ ምርመራ፡
● በጾታዊ ግንኙነት የሚተላለፉ በሽታዎች ምርመራ
● የሽንት ምርመራ
● የልብ ምርመራ
● የሆድ አልትራሳውንድ
● ኮሎኖስኮፒ: ከ50ዓመት ዕድሜ በኋላ (ከዚያ በታች ላሉ በሕክምና ታሪክ ላይ በመመስረት
ሊያስፈልግ ይችላል)
ለሴቶች ተጨማሪ ምርመራዎች
● ማሞግራም
● የኦስቲዮፖሮሲስ ምርመራ (Bone mineral density testing)፡- እድሜያቸው 65 እና ከዛ በላይ
ለሆኑ ሴቶች
● የማህፀን በር ካንሰር ምርመራ
ለወንዶች ተጨማሪ ምርመራዎች
● የፕሮስቴት እና የፕሮስቴት ካንሰር ምርመራ፡ ዕድሜው 50 እና ከዚያ በላይ የሆኑ

Reference:
– Complete Guide to Annual Health Screenings by Age | Columbia NPG
(columbianps.org)
– 2020 Adult Preventive Health Guidelines

EMSA Digital Library

online platform where you can find resources

Fellowship Opportunities

International Opportunities For Young Leaders

ከአእምሮ ጤና ጋር በተያያዘ ድንገተኛ እርዳታ ካስፈለግዎ

በነዚህ ቁጥሮች እርዳታ ያግኙ

Subscribe