የጨቅላ ህፃናት እንከብካቤና ጥንቃቄ ለወላጆች

በተለይ ለመጀመሪያ ጊዜ እናትና አባት የሆኑ ወላጆች ጨቅላ ህፃናት ወደ ቤታቸው ይዘው

ከሄዱ በኋላ እንዴት መንከባከብ እንደለባቸውና ድንገተኛና አሳሳቢ የሆኑ ምልክቶች የቶቹ እንደሆኑ

ለማወቅ አዳጋች ሊሆን ይችላል፡፡ የሚከተሉት ነጥቦች እንዴት መንከባከብ እንደሚቻልና ምን ምን

ምልክቶች  ማየት እንደሚገባ ለማወቅ ይረዳል፡፡

በእንቅልፍ ጊዜ

       ጨቅላ ህፃናት እናታቸው ማህፀን ውስጥ ሳሉ የለመዱትን ድምፅ፣ ሙቀት፣ እንቅስቃሴ እንዲሁም

ብርሃን ካገኙ በሰላም ለመተኛት እና ከነቁም በረጋ ሁኔታ እንዲቆዩ ትልቅ አስተዋጽኦ አለው፡፡ ስለዚህ

ጥሩ ሙቀት እንዲሰማቸው ነገር ግን ላብ እንዳያስችራቸው በመጀመሪያ በንፁህ ደረቅ ካኒቴራ፣ ሱሪ

ካልሲና ኮፍያ አልብሶ ከዚያም በህፃን ብርድልብስ አየር እንዳይገባ አድርጎ በመጠቅለል ሙቀት  መስጠት

ይችላል፡፡ ያሉበት ክፍል ፀጥ ያለ ንፁህ አየር የሚገባበት ብርሃኑ ለአይናቸው እንዳይከብድ ዝቅ ያለ ሲሆን

በሰላም እንቅልፍ ያገኛሉ፡፡

 

 በመመገብ ጊዜ

         ጨቅላ ህፃናት በየ 2-3 ሰዓት ውስጥ እስከ 60 ሚሊ ሊትር የጡትም ሆነ የዱቄት ወተት

ያስፈልጋቸዋል፡፡ ብዙ ጊዜ እንደ ጣት መምጠት፣ አፍ መክፈት ወይም ማልቀስ ምልክት ቢያሳዩም

ተኝተው እንኳን  ቢሆን እየቀሰቀሱ ማጥባት ተገቢ ነው፡፡ ከጠቡም በኋላ ከአንገት ቀና  አድርጎ ደረት

ላይ በመለጠፍ  ወይም በመያዝ ድምፅ አውጥተው እንኪያገሱ መጠበቅ ያስፈልጋል፡፡

 

በፅዳት ጊዜ

 

       ጨቅላ ህፃናት እትብታቸው ደርቆ እስኪወድቅ ድረስ በዋይፐር ወይም በርጥብ ጨርቅ ብቻ

መጠረግ አለባቸው፡፡ ከዚያም በኋላ ለብ ባለ ውሃ ለህፃናት በተመረጡ ለስላሳ ሳሙናዎች በጥንቃቄ

ማጠብ ተገቢ ነው፡፡ የሽንት ጨርቃቸው በየጊዜው እንዳይቆሽሽ በመቀየር ሲቀየርም ቆሻሻው

ሰውነታቸውን እንዳይጎዳ በመጠራረግ ፓውደር በመቀባት መንከባከብ ይመከራል፡፡

 

የማያሳስቡ ምልክቶች

       ጨቅላ ህፃናት በመጀመሪያው ወር አመጋገብ አተነፋፈስ እና እንቅስቃሴ አዲስ ስለሆኑ በተደጋጋሚ

ማቀርሸት/ወደላይ ማለት፣ መጥባት ማስቸገር፣ ቶሎ አለማግሳ፣ ሲተነፍሱ ሲርሲር የሚል ድምፅ መስማት፣

ጭንቅ ያለ አተነፋፈስ፣ አፍንጫ መታፈን፣ በደምብ አለመተኛት እና በተደጋጋሚ ማልቀስ የመሳሰሉት

ምልክቶች ሊታዩ ይችላሉ፡፡ እነዚህ ምልክቶች በጊዜ ስለሚጠፋ ወላጆች ታግሰው በተረጋጋ መንፈስ ማሳለፍ

ደገባቸዋል፡፡

 

ድንገተኛ የሆኑ አሳሳቢ ምልክቶች

 

ወላጆች ቀጥሎ የተዘረዘሩት ምልክቶች ጨቅላ ልጆቻቸው ላይ ሲታይ በአፋጣኝ ወደ ጤና ተቋም ማምጣት

ይኖርባቸዋል፡፡

    . መጥባት ማቆም ወይም በተደጋጋሚ ማስመለስና ማስቀመጥ

    . የፊትና ሰውነት ቢጫ መሆን

    . የሆድ ማበጥና ሰገራ ማስወጣት ማቆም

    ማንቀጥቀጥ

    . የከንፈርና የእግር እጅ ጫፎች ሰማያዊ ወይም ጥቁር ቀለም መያዝ

    . ያለማቋረጥ ማቃሰት በጣም መደካከም

    . በፍጥነትና ደረታቸው ወደውስጥ እስኪገባ መተንፈስ

    . ትኩሳት

    . የእትብት ማበጥ መቅላት ወይም ሳያቋርጥ መድማት

    . የዓይን ቅላትና ቢጫ ፍሳሽ መውጣት፡፡

ለህፃናት ስለሚሰጡ ክትባቶች 

አንድ ህፃን አንድየተወለደ/  በየጊዜው  መወሰድ ያለበት  ክትባቶች ወላጆች አሰታውሰው ማስከተብ አለባቸው፡፡

ክትባት ማለት ለአንድ ለሚተላለፍ በሽታ መከላከያ አስቀድሞ የሚወሰድ መድሀኒት ሲሆን የሰውን የራሱን የመከላከል 

 አቅም በማዳበርና የመከላከያ ኬሚካሎች እንዲያመርት በማድረግ በሽታን ከመምጣቱ በፊት ይከላከላል፡፡                   

 ክትባቶች በአመት 2-3 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች በበሽታ እንዳይያዙ ሲከላከል በበሽታው የተያዙ ሰዎች በአካባቢው   ቢኖሩ እንኳን ወደ ሰውነት ዘልቆ ገብቶ በሽታ እንዳይፈጠር ያደርጋል፡፡

 

የክትባት አሰጣጥ

ክትባቶች ብዙዎቹ በመርፌ መልክ በቆዳ የሚሰጡ  ሲሆኑ አንዳንዶቹ  በአፍ ጠብታ ሊሰጡ ይችላሉ፡፡

 

ክትባት የሚከላከላቸው 7 የህፃናት በሽታዎች 

 

ዲፕቴሪያ(Diptheria)

ይህ በሽታ ወፍራም ፈሳሽ ጉሮሮ ውስጥ በማከማቸትና ሳንባን በማፈንና እንዲሁም ለመተንፈስ በመከልከል                             

የሚያጠቃ ካለታከሙ ለሞት የሚዳርግ በሽታ ነው፡፡

Tetanus (መንጋጋ ቆልፍ)

የሰውነትን ጡንቻ በተለይ የመንጋጋ አካባቢ ያሉ ጡንቻዎችን በማጠንከር መተንፈስ እነዲከብዳቸው ያደርጋል፡፡           

በመንጋጋ ቆልፍ ከሚያዙ 10 ህፃናት አንዱበሞት ይቀጠፋል፡፡

 

Pertusis (ትክትክ)

በጣም ከባድ የሆነ የማያቋርጥ ሀይለኛ ሳል ማስመለስ መተንፈስ  እስኪከብድ ድረስ ሲኖር ትክትክ በሽታ ህፃኑ ሊኖርበት         

  ይችላል፡፡

Measles (ኩፍኝ) /mumps(ጆሮ ደግፍ)MMR

ኩፍኝና  ጆሮ ደግፍ በቫይረስ የሚመጡ በሽታዎች ሲሆኑ የሰውነት ላይሽፍታዎችና ማሳከክ ሊኖር ይችላል፡፡ አንገት ስር           

 በግራና በቀኝ ከትኩሳትና ከህመም ጋር የተያያዘ እብጠት ሲኖር ደግሞ የጆሮ ደግፍ ምልክቶች

ናቸው እነዚህ በሽታዎች ብዙ ጊዜ ለህይወት የሚያሰጉ በሽታዎች ባይሆኑም ህፃናቶችን

እንዲሁም ትንንሽ ልጆችን ያሰቃያሉ፡፡

የህፃናት የሳንባ ምች (pnemocucus ,H.lnfluenza)Hib

አንድህፃን በተለይ 5 አመት በታች  ሆኖ ራስምታት ሳልና የአተነፋፈስ ችግር ካለበት የሳንባምች በሽታ የተያዘ ሊሆን ይችላል               

 ይህንን አደገኛ በሽታ ለመከላከል የሚጠቅሙክትባቶችን ገና በልጅነቱ ካገኘ ግን ከነዚህ በሽታዎች ይጠበቃል፡፡

ሄቨታይተስ (hepatitis B)

የአይን ወይም የሰውነት ቢጫ መሆንና ተቅማጥ ማስመለስ መደካከም የጡንቻዎች የመገጣጠሚያ ወይም ሆድ ህመም የሄቨታይተስ               

በሽታ በህፃናት ሲከሰቱ ከምናያቸው ምልክቶች ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡

ፖሊዮ (polio) OPV

ይህ በሽታ በተለይ እንደኛ አይነት ሶስተኛ አለም አገራት የእግር አፈጣጠር ችግር ከሚያመጡ ምክንያቶች ውስጥ አንዱ ሲሆን በክትባት

መከላከል የሚቻል ክምድረገፅ ሊጠፋ የተቃረበ በሽታ ነው፡፡

 

የክትባት አሰጣጥ ጊዜ ፕሮግራም

 የክትባት የጎንዮሽ ምልክቶች

አንድ ህፃን ክትባት ሲከተብ ከበሽታው ከራሱ የተሰራ መከላከያ በመሆኑ የጎንዮሽ አንዳንድ የማያሳስቡ ምልክቶች ሊኖሩ                 

 ይችላሉ፡፡ ለምሳሌ

    . መጠነኛ ትኩሳት

    . የተከተበበት ቦታ ማበጥ ሲነካ ማመም ቀይመሆን

    . መደካከም የምግብ ፍላጎት መቀነስ

    . ማስመለስ

ምናልባት የሚያሳስቡና በፍጥነት ወደ ጤና ተቋም ሊያመጡ የሚገባቸው ምልክቶች

    . ማዞር እጅግ መደካከም

    . ማንቀጥቀጥ

    . ሰውነት ላይ ሽፍታ መውጣት

    . የፊት ጉሮሮ ጋር ማበጥ መተንፈስ መክበድ

 

 

 

 

 

EMSA Digital Library

online platform where you can find resources

Fellowship Opportunities

International Opportunities For Young Leaders

ከአእምሮ ጤና ጋር በተያያዘ ድንገተኛ እርዳታ ካስፈለግዎ

በነዚህ ቁጥሮች እርዳታ ያግኙ

Subscribe