ተጨማሪ ጽሁፎች

ከአልኮል ጋር የተያያዘ የጉበት ህመም

  በዶ/ር ቃልኪዳን ጫላ (የውስጥ ደዌ ስፔሻሊስት ሀኪም)   አልኮልን አብዝቶ መውሰድ ለተለያዩ የጤና ጉዳቶች እንደሚዳርግ ይታወቃል። ከነዚህም አንዱና ዋነኛው ከአልኮል ጋር የተያያዘ የጉበት ህመም የምንለው ነው። አልኮል ከሰውነታችን ውስጥ የሚወገደው በጉበት አማካኝነት ነው። ስለዚህም ለረጅም አመታት አልኮልን መጠጣት ወይንም አልፎ አልፎ ከመጠን ባለፈ መልኩ መውሰድ ለጉበት ህመም ይዳርጋል። የአልኮል ጉዳት ከመጠን ጋር የተያያዘ እንደሆነ ጥናቶች […]

የማህፀን በር ጫፍ ካንሰር ሳይከሰት ቀድሞ መከላከል ይቻላል ፡፡

የማህፀን በር ጫፍ ካንሰርየቅድመ ካንሰር ምርመራ (ህዋሶች ) ከተለመደው ወጣ ባለ እና ጤናማ ባልሆነ መልኩ ሲያድጉ እና ሲባዙ ይፈጠራል ።  የማህጸን በር ካንሰር በማህጸን አካባቢ ያሉ የሰውነት ክፍሎችን ሊወር፣ ወደሌላ የሰውነት ክፍሎቻችንም ሊሰራጭ ይችላል በአለማችን ያሉ ሴቶችን በብዛት ከሚያጠቁ የካንሰር በሽታዎች አራተኛውን ደረጃ የያዘው የማህፀን ጫፍ ካንሰር የሚባለው የካንሰር ዓይነት ነው፡፡ ይህን በሽታ ለየት የሚያደርገው […]

ቅድመ ወሊድ እና በ እርግዝና ጊዜ የ ሚያስፈልገን ክትትል።

በእርግዝና ጊዜ የተለመዱ የህመም ምልክቶች በእርግዝና ጊዜ የተለመዱ የህመም ምልክቶቸ የቶቹ ናቸው ?          ከእርግዝና ጋር ተያይዞ የተለያዩ ለውጦች በሰውነት ላይ ይከሰታሉ፡፡ ይህም የሚሆነው የሰውነት ሆርሞኖችና የስራ ሂደቶች ስለሚጨመሩ ነው፡፡   በሰውነት ላይ የሚፈጠረው ጫና አንዳንድ የህመም ምልክቶች ሊያመጣ ሲችል ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ዋናዎች ናቸው፡፡ የድድ መድማት         ድዳችን […]

የጨቅላ ህፃናት እንከብካቤና ጥንቃቄ ለወላጆች

በተለይ ለመጀመሪያ ጊዜ እናትና አባት የሆኑ ወላጆች ጨቅላ ህፃናት ወደ ቤታቸው ይዘው ከሄዱ በኋላ እንዴት መንከባከብ እንደለባቸውና ድንገተኛና አሳሳቢ የሆኑ ምልክቶች የቶቹ እንደሆኑ ለማወቅ አዳጋች ሊሆን ይችላል፡፡ የሚከተሉት ነጥቦች እንዴት መንከባከብ እንደሚቻልና ምን ምን ምልክቶች  ማየት እንደሚገባ ለማወቅ ይረዳል፡፡ በእንቅልፍ ጊዜ        ጨቅላ ህፃናት እናታቸው ማህፀን ውስጥ ሳሉ የለመዱትን ድምፅ፣ ሙቀት፣ እንቅስቃሴ እንዲሁም ብርሃን ካገኙ […]

አመታዊ የጤና ምርመራ

አመታዊ የጤና ምርመራ በተለያየ የዕድሜ ክልል ላይ ላሉ ሰዎች የሚደረግ እና ለአንድ በሽታ የመጋለጥ እድላቸውን ቀድሞ ለማወቅ የሚያስችል የምርመራ ዘዴ ነው። እድሜ እና ፃታን መሠረት አድርገው በየአመቱ እና ከዛም በላይ ሊደረጉ የሚገቡ የምርመራ አይነቶች አሉ። እነዚህን ምርመራዎች መረዳት እና መቼ መጠየቅ እንዳለቦት ማወቅ ጤናማ ሆነው እንዲቆዩ ያግዝዎታል። እንደ ካንሰር እና አንዳንድ በቅድመ ጥንቃቄ ልንከላከላቸው የምንችላቸውን […]

የመተንፈሻ ማሽን (Mechanical Ventilator)

በዶ/ር ናታን ሙሉብርሃን  (የድንገተኛና ጽኑ ህክምና ስፔሻሊስት ) መቼም የኮሮናን ወረርሽኝ ተከትሎ ስለመተንፈሻ ማሽን አስፈላጊነትና ጥቅም ተደጋግሞ ሲነገር መስማት የተለመደ ሆኗል። ለመሆኑ የመተንፈሻ ማሽን (Mechanical Ventilator) ምንድነው? እንዴትስ ይሰራል? መቼስ ነው የምንጠቀመው? እነሆ ብያለሁ… የሰው ልጅ ለመኖር ከሚያስፈልጉት ንጥረ ነገሮች መካከል ኦክስጅን ቀዳሚ ሊባል የሚችል ሲሆን ይህንንም ከከባቢ አየር ላይ አየር በአፍንጫና አፍ በኩል ተስቦና […]

የአስም ህመም መባባስ

በዶ/ር ናታን ሙሉብርሃን (የድንገተኛ እና ፅኑ ህክምና ስፔሻሊስት) የክረምቱን መግባት ተከትሎ ሊባባሱ ከሚችሉ የመተንፈሻ አካላት ህመም አንዱ አስም ነው። አስም የታችኛው የአየር ቱቦን የሚያጠቃ ህመም ሲሆን በተራዘመ የጊዜ ሂደት (chronic) የአየር ቱቦ መቆጣት ሳቢያ የሚከሰት ነው። በአለማችን ላይ 300 ሚሊዮን ሰዎች የአስም ህመም ታማሚ ሲሆኑ በአጣዳፊ የአስም ህመም ምክንያት እጅግ ብዙ ሰዎች በየአመቱ ድንገተኛ ክፍል […]

የቅድመ ቀዶ ህክምና ዝግጅቶች

በዶ/ር ኤደን በላይ (በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የቀዶ ህክምና ስፔሻላይዜሽን ሬዚደንት)     ማንኛውም ታካሚ የቀዶ ህክምና እንደሚያስፈልገው በሃኪሙ ከተነገረው በኃላ ከህክምናው አስቀድሞ አስፈላጊው ዝግጅት መደረግ አለበት:: ከቀዶ ህክምናዎ በፊት በሃኪምዎ የሚታዘዙ ምርመራዎችና አንዳንድ ቅድመ ጥንቃቄዎች እንደ ኦፕሬሽኑ አይነትና ውስብስብነት ሊለያዩ ቢችሉም ከማንኛውም ቀዶ ህክምና በፊት መሰረታዊ የደም ምርመራዎች፣ የህመሙን ምንነትና ደረጃ ለመረዳት የሚያግዙ እንደ […]

የልብ ድካም

በዶ/ር ናታን ሙሉብርሃን (የድንገተኛ እና ፅኑ ህክምና ስፔሻሊስት ሀኪም)     የልብ ድካም በአለማችን ቁጥር አንድ ገዳይ በሽታ ነው። በአለማችን ላይ በአመት ወደ ሰባት ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች በልብ ድካም ሳቢያ ህይወታቸውን የሚያጡ ሲሆን በሃገራችንም ቁጥሩ ከጊዜ ወደ ጊዜ በአሳሳቢ መልኩ እየጨመረ ይገኛል።  የልብ ድካም ሲከሰት ወደ ልብ ጡንቻ የሚዘዋወረው ደም በከፊል ወይም ሙሉ ለሙሉ የሚቋረጥ […]

የቶንሲል ኢንፌክሽን እና የሪዉማቲክ የልብ በሽታ

በዶ/ር ትዕግስት ስለሺ (የውስጥ ደዌ ስፔሻሊስት እና የልብ ሰብ ስፔሻሊቲ ፌሎው)  የሪውማቲክ የልብ ህመም በአለም ላይ እስከ 30 ሚሊዮን በሚጠጉ ሰዎች  አብዛኞቹም በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ባሉ ሃገራት ይገኛል ።  ከእነዚህም መካከል በአመት ዉስጥ ወደ 275,000 ሰዎችን ለሞት ይዳርጋል።     በአብዛኛው ከ 5 እስከ 15 አመት የእድሜ ክልል ዉስጥ ያሉ ህፃናት እና ታዳጊዎችን የሚያጠቃ ሲሆን ከፆታ […]